በሆዱ ይሰድበኛል?

ከቀናት መካከል ከእለታቱ አንዱ

ነበሩ ሁለት ልጆች የማይዋደዱ::

እህት ወንድም ሆው ካንድ እናት ካንድ አባት

ሁል ጊዜ ጠብ ሆነ ጠፋና መስማማት::

ወላጅ እናታቸው መፍትሄ ብታጣ

አንዱን በግራዋ አንዱን ቀኝ አስቀምጣ

"ከዚህች ሰዓት ውዲህ አንዲት

ድም እንዲ ልስማ" አለች ተቆጥታ።

ብዙም ጊዜ ላይቆይ ደቂቃም ሣይሞላ

ትንሽቷ ልጂ ወ ኧሪ ብላ

ታለቅስ ጀመረ ከልቧ አምራ :

አን ምን ሆንኩ ብለሽ ነው የምታለቅሺ፣

ካፉ ቃል አልወጣ አልደረሰብሺ?"

ብላ ብትጠይቃት እናት ግራ ገብቷት

እንባ እያጎረፈች ትንፋሽ እያጠራት

"በሆዱ ይስድበኛል" ብላ ነገረቻት ::

በአእምሮችን ምላስ ትንሽ ብናጣጥም

ቅኔ ሲነገረን በወርቅና በስም

ከዚህች ምሳሌ ሳንማር አንቀርም።

በታ ቤት ስንኖር እንደ እህት ወንድም

ከስንት አንድ ጊዜ ባሣብ ባንጣጣም

ይህ ያለ ነውና ፍፁም አይርመኝም:

እኔን የሚገርመኝ አልባ የሚለኝ

በዳይ በሌለበት ተበደልኩ ባይ ሲኝ:

በራችን ሃሣብ ጥላ ስንደነበር

ገና ሣይደርሰብን ሣይነግሩብን ነር

ሳንረዳ ሃሣቡን ንቀርበው ናውቀው

ስንቱን ወንድማችን በሩቁ ጠላነው:

እንደወትሮው ሰላም ባይል ሃሣብ ገብቶት

የከበደ ሃዘን ደርሶበት ምናልባት

ችግሩ ከእኛ ጋር ካልሆነ በስተቀር፣

ከሰላምታ አቅም አይነፍኝም ነበር::''

ብለን ካከበደን ካከረርን ነገር

ቀስ ብላ አድጋ ይህቺ መራራ ስር

ቂም ቁርሾ አይላ ስታባርር ፍቅር

ከዚያ በኋላማ ምን ሰላም ይኖራል

እንደምን አደርከም ስድብ ይሆንብናል።

በሙሴ ወንበር ላይ ወጥተን ጉብ ብለን

አንዱን በኤል ዘቤል አንዱን መላክ አርን

ከኮነን ካጸደቅን ብተን ከፍርድ ተራ

ክንዱ ባይገለጥ መንፈሱ ባይሰራ

ምን ያስደንቀናል

እሾህ ከተከልን በለስ አያፈራ:

ህሊናችን ነፅቶ በደሙ ተረጭቶ

ለእኛም እንደዳዊት ንፁህ ልብ ፈጥሮልን

ወንድም ህታችን ዘወትር ታግሰን

ለመለየት ሳይሆን ለፍቅር ምክንያት ፈጥረን

የጠፋን ፈላጊ የራቀን አቅራቢ

እንድንሆን ያድርን

የመስቀሉን ፍቅር ጌታ ያለማምደን::

ከግዛቸው ወርቁ

Previous
Previous

ለሞት እንዳልተኛ አይኖቼን አብራ

Next
Next

ካንተ ወዴት ይሸሻል?